____Welcome to Central Ethiopia Region Planning and Development Bureau____
እንኳን ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክል መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ኦፊሴላዊ ድህረ ገጽ በደህና መጡ! የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ መልክ ሲቋቋም የክልሉን አስፈፃሚ አካላትን ስልጠንና ተግባር ለመወሰን በክልል ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 መሠረት ከተቋቋሙ የክልል ተቋማት አንዱ ነው፡፡
ቢሮው የክልሉን መንግስት የረጅም፣የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅዶችን በማዘጋጀት እና ዕቅዶቹን ለማዘጋጀት የሚረዱ የኢኮኖሚ ጥናቶችን እና ምርምር በማካሄደ፣ አፈጻጸምን ለመለካት ኢኮኖሚዊ እና ማህበራዊ አመልካቾችን በማዘጋጀት እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የቴክኖሎጂ ልማት ማዕቀፎችን በመፍጠር እና በመተግበር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ስለ ክልላዊ የልማት እና የመልካም አስተዳደር እና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች፣ የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ እንዲሁም የፕሮጀክት ዕቅዶች እና የአፈጻጸም ሁኔታ ወቅታዊ እና የተገመገሙ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ያሉትን የአስተዳደር ደረጃዎች ካርታዎች፣ የክልሉን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስርጭት፣ የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና መልክአ ምድራዊና የክልሉን ሙሉ መገለጫ እና የክልሉ የታችኛው የአስተዳደር ዕርከን ዓመታዊ የሀብት(በጀት) ማከፋፈያ ቀመር ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የዋሉ መረጃዎችን ያገኛሉ፤
ስለ ክልላዊ ጠቅላላ የምርት እድገት መጠን፣ በኢኮኖሚ ዘርፎች የተጨመረውን እሴት መጠን እና ከጠቅላላ ምርት ድርሻ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ክልላዊ ዕቅድ እና ሪፖርቶች የአሠራር ደንቦችን እና መመሪያዎችን እንዲሁም የስነ ህዝብ ጥናቶችን እና ተያያዥ ወቅታዊ መረጃዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ ዝግጁ ነን፡፡ ስለዚህ ድህረ ገጻችንን እንዲጎበኙ እና የሰጠነውን መረጃ እንዲያገኙ እንጋብዝዎታለን፡፡ስለ ይዘቱ እና ስለ ድህረ ገጹ ለሰጡን አስተያየት እናመሰግናለን፡፡
አቶ ዳንኤል ዳምጠው አንጭሶ
የቢሮ ኃላፊ
Latest News
The Higher Officials of Bureau
የቢሮ ኃላፊ |
ምክትል ቢሮ ኃላፊና የማክሮ ኢኮኖሚ ዕቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዘርፍ |
ምክትል ቢሮ ኃላፊና የልማት መረጃ አስተዳደርና ስነ ህዝብ ጉዳዩች ዘርፍ ኃላፊ |
Stakeholders
Explore more
Google Location




